ASPA | African Studies Professionals Association

ASPA | African Studies Professional Association

የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ የአፍሪካ ማዕከል ርክክብን የሚዲያ ሽፋን መጠየቅን ይመለከታል

የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ የአፍሪካ ማዕከል ርክክብን የሚዲያ ሽፋን መጠየቅን ይመለከታል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘውን አዲሱ የአፍሪካ ማዕከል ከፍተኛ የመንግስታቱ ድርጅት ኃላፊዎች፣ የአ.አ.ዩ. አመራሮች፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ሀገራት ኤምባሲ ተወካዮች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ይካሄዳል።

ማዕከሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተቀየሱ የልማት ግብዎችን ለመተግበር እና በአፍሪካ አህጉር ዘላቂ ልማትን ለማስመዝገብ የሚረዱ ጥናት እና ምርምሮችን ለማከናወን የሚረዳ ሲሆን፤ እንደ አህጉር 54 ሀገራትን በመወከል በኢትዮጵያ የሚገኝ ብቸኛ ተቋም ነው።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የአፍሪካ እና እስያ ጉዳዮች ጥናት ማዕከል በማቋቋም የሁለተኛ እና የ3ኛ ድግሪ ተማሪዎች በማስተማር የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ እውቀት መር እንዲሆን የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል።

የአፍሪካ እና እስያ ጉዳዮች ጥናት ማዕከል ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ ይረዳው ዘንድም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጄፍሪ ሳክስ በ38ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአ.አ.ዩ. ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እና የኢፌዴሪ የመንግስት ተጠሪ ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር) የጋራ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። ማዕከሉ ኢትዮጵያ የአለማቀፍ ተቋማት መገኛ መሆኗን፤ ቀድሞ በርዎንዳ የነበረው ማዕከል መዘጋትን ተከትሎ የሚከፈት በመሆኑ የሀገራችንን የዲፕሎማሲ ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል ተብሎ ይታመናል።

በመሆኑም አዲሱ የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ የአፍሪካ ማዕከል በአ.አ.ዩ. ዋናው ግቢ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ራስ መኮንን አዳራሽ ሰኞ የካቲት 10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ርክክቡ ይከናወናል። ስለሆነም በዕለቱ በመገኘት የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡልን በአክብሮት እንጠይቃለን።